ከእኛ እያንዳንዳችን የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን በማስረከብ፥ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እናደርጋለን፤ እንዲሁም ከላሞቻችን፥ ከበጎቻችንና ከፍየሎቻችን የሚወለደውንም ጥጃና ግልገል ሁሉ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር እንለያለን።
ገላትያ 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃሉን የሚማር ሰው ከአስተማሪው ጋር መልካሙን ነገር ሁሉ ይካፈል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም ቃሉን የሚማር፣ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ከመምህሩ ጋራ ይካፈል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሉን የሚማር መልካሙን ነገር ሁሉ ከሚያስተምረው ጋር ይካፈል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ነገር ንኡሰ ክርስቲያን ይስማው፤ መልካሙንም ነገር ሁሉ ከሚያስተምረው ይማር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል። |
ከእኛ እያንዳንዳችን የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን በማስረከብ፥ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እናደርጋለን፤ እንዲሁም ከላሞቻችን፥ ከበጎቻችንና ከፍየሎቻችን የሚወለደውንም ጥጃና ግልገል ሁሉ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር እንለያለን።
እርሱ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለምትሰጡት አገልግሎት የድካም ዋጋችሁ ስለ ሆነ የተረፈውንም እናንተና ቤተሰቦቻችሁ በየትኛውም ስፍራ ሆናችሁ መመገብ ትችላላችሁ፤
ይህንንም ርዳታ በፈቃደኛነት የለገሡት ግዴታቸው በመሆኑ ነው፤ አሕዛብ ከአይሁድ ጋር የመንፈስ በረከት ተካፋዮች ከሆኑ እነርሱም በሥጋዊ በረከታቸው አይሁድን የመርዳት ግዴታ አለባቸው።