እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
ገላትያ 5:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሥጋ ምኞት ከመንፈስ ምኞት ጋር ይቃረናል፤ መንፈስና ሥጋ እርስ በእርሳቸው ይቃረናሉ፤ ስለዚህ እናንተ የምትፈልጉትን ማድረግ አትችሉም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋ መንፈስ የማይፈልገውን፣ መንፈስም ሥጋ የማይፈልገውን ይመኛልና፤ እነዚህ እርስ በርሳቸው ስለሚጋጩ፣ የምትፈልጉትን አታደርጉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋ መንፈስ የማይፈልገውን ይመኛል፥ መንፈስም ሥጋ የማይፈልገውን፤ እነዚህ እርስ በርሳቸው ስለሚቀዋወሙ የምትፈልጉትን ማድረግ አትችሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋ መንፈስ የማይሻውን ይሻልና፥ መንፈስም ሥጋ የማይሻውን ይሻልና፥ የምትሹትንም እንዳታደርጉ እርስ በርሳቸው ይጣላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። |
እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
ኢየሱስ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን፦ “አንተ ሰይጣን! ከኋላዬ ሂድ! አንተ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር ስለማታስብ ለእኔ እንቅፋት ነህ” አለው።
እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? ከቶ አይቃወምም! ሕይወት የሚገኝበት ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ጽድቅ በሕግ አማካይነት በተገኘ ነበር።