ገላትያ 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቼ ሆይ! እኔ እስከ አሁን የምሰብከው “ለመዳን መገረዝ ያስፈልጋል” እያልኩ ቢሆን ኖሮ እስከ አሁን ለምን ያሳድዱኝ ነበር? እንዲህ ቢሆን ኖሮ የክርስቶስ መስቀል ለሰዎች እንቅፋት መሆኑ ይቀር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ እስከ ዛሬ ስለ መገረዝ የምሰብክ ከሆነ፣ ታዲያ እስከ አሁን ለምን ያሳድዱኛል? እንደዚያማ ቢሆን ኖሮ፣ መስቀል ዕንቅፋት መሆኑ በቀረ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! እስከ አሁን መገረዝን ብሰብክ ኖሮ ታዲያ እስከ አሁን ድረስ ለምን ያሳድዱኛል? ስለዚህ የመስቀል እንቅፋትነት ይቀር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ግዝረትን ገና የምሰብክ ከሆነ፥ እንግዲህ ለምን ያሳድዱኛል? እንግዲህ የክርስቶስ የመስቀሉ ተግዳሮት እንዲያው ቀርቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እስከ አሁን መገረዝን ብሰብክ እስከ አሁን ድረስ ለምን ያሳድዱኛል? እንኪያስ የመስቀል ዕንቅፋት ተወግዶአል። |
ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ይዞ መሄድ ስለ ፈለገ በዚያ ስፍራ በነበሩት አይሁድ ምክንያት እንዲገረዝ አደረገው፤ ይህንንም ያደረገው እነርሱ የጢሞቴዎስ አባት አረማዊ መሆኑን ያውቁ ስለ ነበረ ስለ እነርሱ ብሎ ነው።
አንተ በአሕዛብ መካከል የሚኖሩትን አይሁድ ሁሉ ‘ልጆቻችሁን አትግረዙ ወይም ሥርዓቶችን አትፈጽሙ’ እያልክ በማስተማር የሙሴን ሕግ እንዲሽሩ ታደርጋለህ እየተባለ የሚወራውን ሰምተዋል።
“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! እርዱን! ሕዝባችንንና ሕጋችንን፥ ይህንንም ስፍራ እየተሳደበ በየአገሩ ያለውን ሕዝብ ሁሉ የሚያስተምር ይህ ሰው ነው፤ ይህም አልበቃ ብሎት አሕዛብን ወደ ቤተ መቅደስ በማስገባት ይህን የተቀደሰ ስፍራ አርክሶአል!” እያሉ ጮኹ።
እናንተ ሞኞች የገላትያ ሰዎች! ማን አፍዝ አደንግዝ አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ በፊት ለፊታችሁ በግልጥ ይታይ ነበር።
እንድትገረዙ የሚያስገድዱአችሁ በውጭ መልካም መስለው ለመታየት የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። ይህን የሚያደርጉትም በክርስቶስ መስቀል ምክንያት ስደት እንዳይደርስባቸው ብለው ነው።