ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
ገላትያ 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድን እምነት በመጠበቅ በዘመኔ ከነበሩት ከብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቼ ሁሉ እበልጥ ነበር፤ ስለ አባቶችም ወግ ከፍተኛ ቅናት ነበረኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ዕድሜ ዘመን ከነበሩት ከብዙዎቹ አይሁድ ይበልጥ በአይሁድ ሃይማኖት እልቅ ነበር፤ ስለ አባቶቼም ወግ እጅግ ቀናተኛ ነበርሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአባቶች ወግ ከመጠን በላይ ቅናት ስለ ነበረኝ፥ በአይሁዳዊነት ወገኖቼ ከነበሩት እኩዮቼ ብዙዎችን እበልጥ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአባቶች ሥርዐት እጅግ ቀናተኛ ነበርሁና በወገኖች ዘንድ ከጓደኞች ሁሉ በአይሁድ ዘንድ እጅግ ከበርሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአባቶችም ወግ ከመጠን ይልቅ እየቀናሁ በወገኔ ዘንድ በዘመኔ ካሉት ብዙዎችን በአይሁድ ሥርዓት እበልጥ ነበር። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
‘ታዲያ ወዴት እንሂድ?’ ብለው ቢጠይቁህ፥ ከዚህ በፊት እንዲህ ብዬ የነገርኳቸውን አስታውሳቸው፤ ‘በመቅሠፍት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በመቅሠፍት ይሞታሉ! በጦርነት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በጦርነት ይሞታሉ! በራብ እንዲሞቱ የተፈረደባቸውም በራብ ይሞታሉ። ተማርከው እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው ወደ ምርኮ ይሂዱ።’
‘ያ ሰው አባቱን [ወይም እናቱን] ማክበር አያስፈልገውም’ ትላላችሁ፤ ስለዚህ ወጋችሁን ለማጥበቅ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ሕግ ታፈርሳላችሁ፤
ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም ጌታን አመሰገኑ፤ ጳውሎስንም እንዲህ አሉት፦ “ወንድም ሆይ! በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ምእመናን በአይሁድ መካከል እንዳሉና ሁሉም ለሕግ ቀናተኞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፤
“እኔ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ ከተማ የተወለድኩ አይሁዳዊ ነኝ፤ ያደግኹት ግን በዚህች በኢየሩሳሌም ከተማ ነው። አስተማሪዬም ገማልያል ነበር፤ የአባቶችን ሕግ ጠንቅቄ የተማርኩና ልክ ዛሬ እናንተ እንደምታደርጉት እግዚአብሔርን በመንፈሳዊ ቅናት የማገለግል ነበርኩ።
በክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በሰው ሠራሽ ወግና በዓለማዊ ተራ ሥርዓት ላይ በተመሠረተ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳያጠምዳችሁ ተጠንቀቁ።
ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።