ከዚህ በኋላ አገረ ገዢው ታተናይ፥ ሸታርቦዝናይና የእነርሱም ተባባሪዎች የሆኑ ባለሥልጣኖች ንጉሠ ነገሥቱ እንዳዘዛቸው ሁሉንም ነገር ፈጸሙ።
ዕዝራ 8:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሠ ነገሥቱ የሰጣቸውንም ሰነድ በኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ላሉት ገዢዎችና ባለሥልጣኖች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ በማገዝ ድጋፋቸውን ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሡንም ትእዛዝ ለንጉሡ እንደራሴዎችና በኤፍራጥስ ማዶ ለሚገኙት አገረ ገዦች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት ረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሡንም ትእዛዝ በወንዝ ማዶ ላሉት ለንጉሡ እንደራሴዎችና ገዢዎች ሰጡ፥ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት አገዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሡንም ትእዛዝ በወንዙ ማዶ ላሉት ለንጉሡ ሹሞችና ገዢዎች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት አከበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንጉሡንም ትእዛዝ በወንዝ ማዶ ላሉት ለንጉሡ ሹማምቶችና ገዦች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት አገዙ። |
ከዚህ በኋላ አገረ ገዢው ታተናይ፥ ሸታርቦዝናይና የእነርሱም ተባባሪዎች የሆኑ ባለሥልጣኖች ንጉሠ ነገሥቱ እንዳዘዛቸው ሁሉንም ነገር ፈጸሙ።
ከዚያም በመቀጠል ወደ ይሁዳ ማለፍ እንዲፈቅዱልኝ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ክፍለ ሀገር ላሉት አገረ ገዢዎች የይለፍ ደብዳቤ እንዲሰጠኝ ለንጉሠ ነገሥቱ ልመና አቀረብኩ፤
ስለዚህ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ሃማን የንጉሡን ጸሐፊዎች ጠርቶ ዐዋጁ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተተርጒሞ፥ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በሚገኘው የአጻጻፍ ሥርዓት ሁሉ በመዘጋጀት፥ ወደ አገረ ገዢዎችና ወደ ባለሥልጣኖች ሁሉ እንዲላክ ያደርጉ ዘንድ አዘዘ፤ ዐዋጁም በንጉሥ አርጤክስስ ስም ተጽፎ የቀለበቱ ማኅተም ተደርጎበት ተላለፈ።
እንዲያውም የየሀገሩ ገዢዎችና አስተዳዳሪዎች ሌሎችም ባለሥልጣኖችና የመንግሥት ተወካዮች ሁሉ አይሁድን ረዱአቸው፤ ይህንንም ያደረጉት መርዶክዮስን በመፍራት ነበር።
አጵሎስ ወደ አካይያ ለመሄድ ባሰበ ጊዜ ወንድሞች አሳቡን ደገፉ፤ በአካይያ ያሉ ወንድሞች በመልካም ሁኔታ እንዲቀበሉትም ደብዳቤ ጻፉለት። እዚያም በደረሰ ጊዜ በእግዚአብሔር ጸጋ አማኞች ለመሆን የበቁትን በጣም ረዳቸው።