ለሰሎሞን የጒልበት ሥራ ይሠሩለት የነበሩት የግዳጅ ሥራ ሠራተኞች እስራኤላውያን ምድራቸውን ርስት አድርገው በወረሱ ጊዜ ያልገደሉአቸው የከነዓን ሕዝብ ትውልዶች ነበሩ፤ እነዚህም ትውልዶች እስከ አሁን ድረስ ባሪያዎች ሆነው የሚያገለግሉ አሞራውያን፥ ሒታውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
ዕዝራ 2:55 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰሎሞን አገልጋዮችም ወገን ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች፥ ሶጣይ፥ ሀሶፌሬት፥ ፐሩዳ፥ ያዕላ፥ ዳርቆን፥ ጊዴል፥ ሸፋጥያ፥ ሐጢል፥ ፖኬሬት፥ ሐጸባይምና አሚ ተብለው የሚጠሩ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦ የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰሎሞንም አገልጋዮች ልጆች፦ የሶጣይ ልጆች፥ የሃሶፌሬት ልጆች፥ የፕሩዳ ልጆች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች፤ የሳጢ ልጆች፥ የሰፌርታ ልጆች፥ የፋዱርሓ ልጆች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥ |
ለሰሎሞን የጒልበት ሥራ ይሠሩለት የነበሩት የግዳጅ ሥራ ሠራተኞች እስራኤላውያን ምድራቸውን ርስት አድርገው በወረሱ ጊዜ ያልገደሉአቸው የከነዓን ሕዝብ ትውልዶች ነበሩ፤ እነዚህም ትውልዶች እስከ አሁን ድረስ ባሪያዎች ሆነው የሚያገለግሉ አሞራውያን፥ ሒታውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
ከምርኮ የተመለሱ የሰሎሞን አገልጋዮች ጐሣዎች፦ ሶጣይ፥ ሶፌሬት፥ ፐሪዳ፥ ያዕላ፥ ዳርቆን፥ ጊዴል፥ ሸፋጥያ፥ ሐጢል፥ ፖኬሬት ሀጸባይምና አሞን።
ወንዶችና ሴቶች ባርያዎችን ገዛሁ፤ ሌሎች የቤት ውልድ አገልጋዮችም ነበሩኝ፤ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ብዙ የከብት፥ የፍየልና የበግ መንጋ አረባሁ።