ዳዊት እነዚህን ሁሉ ለገባዖን ሰዎች አሳልፎ ሰጠ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት በተራራው ላይ ሰቀሉአቸው፤ ሰባቱም በአንድነት ሞቱ፤ እነርሱም የተገደሉት በጸደይ ወራት ማለቂያና በገብስ መከር መጀመሪያ ላይ ነበር።
ዘፀአት 9:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገብስ ገና እሸት፥ ተልባውም ገና በማበብ ላይ ስለ ነበር አንድም ሳይቀር በሙሉ ተበላሸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተልባው አብቦ፣ ገብሱም ፍሬ ይዞ ስለ ነበር፣ ተልባውና ገብሱ ከጥቅም ውጭ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገብሱና ተልባው ተመታ፤ ገብሱ ገና እሸት ተልባውም እንቡጥ ስለ ነበረ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተልባውና ገብሱ ተመታ፤ ገብሱ አሽቶ፥ ተልባውም አፍርቶ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገብሱ አሽቶ ተልባውም ኣፍርቶ ነበርና ተልባና ገብሱ ተመታ። |
ዳዊት እነዚህን ሁሉ ለገባዖን ሰዎች አሳልፎ ሰጠ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት በተራራው ላይ ሰቀሉአቸው፤ ሰባቱም በአንድነት ሞቱ፤ እነርሱም የተገደሉት በጸደይ ወራት ማለቂያና በገብስ መከር መጀመሪያ ላይ ነበር።
“ሰብላችሁን የሚያደርቅ ብርቱ ነፋስ ላክሁባችሁ፤ አትክልታችሁንና የወይን ተክላችሁን የበለስና የወይራ ዛፋችሁን ሁሉ አንበጣ በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፥ በወይን ተክል ላይም ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ዛፍም ምንም ፍሬ ባይሰጥ፥ በእርሻዎች ላይ ሰብል ቢጠፋ፥ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፥ በበረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፥
እንግዲህ ናዖሚ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር ከሞአብ አገር የተመለሰችው በዚህ ሁኔታ ነበር፤ እነርሱ ቤተልሔም በደረሱ ጊዜ የገብስ መከር የሚሰበሰብበት ወቅት መጀመሩ ነበር።
ስለዚህ ሩት የገብሱና የስንዴው መከር ተሰብስቦ እስኪያበቃ ድረስ በቦዔዝ ገረዶች አጠገብ እየቃረመች ቈየች፤ ከዐማትዋም ሳትለይ አብራ ተቀመጠች።