ዘፀአት 6:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤልን ሕዝብ ልቀቅ” ብለው ከግብጽ ንጉሥ ጋር የተነጋገሩ እነርሱ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ እስራኤላውያን ከግብጽ መውጣት፣ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ያናገሩትም እነዚሁ ሙሴና አሮን ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ስለማውጣት የተነጋገሩ ናቸው፤ እነዚህም ሙሴና አሮን ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ያወጡ ዘንድ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የተነጋገሩ ናቸው፤ እነዚህም ሙሴና አሮን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ የእስራኤልን ልጆች “ከግብፅ ያወጡ ዘንድ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የተነጋገሩ ናቸው፤ እነዚህ ሙሴና አሮን ናቸው። |
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተና ከግብጽ ምድር መርተህ ያወጣኻቸው ሕዝብ ሁሉ ከዚህ ሰፈር ተነሥታችሁ፥ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለተወላጆቻቸው ጭምር ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ሂዱ።
እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን “እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር መርታችሁ እንድታወጡ እኔ ያዘዝኳችሁ መሆኔን ለእስራኤላውያንና ለግብጽ ንጉሥ ንገሩ” ብሎ አዘዛቸው።
ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት በጣለው ጊዜ ተለውጦ እባብ ሆነ።
ሳሙኤልም የሚናገረውን ቃል በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፥ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ምድር ያወጣ እግዚአብሔር ነው፤