ዘፀአት 5:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆችም ወደ ንጉሡ ቀርበው “ንጉሥ ሆይ፥ በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ እንዴት ይህን ሁሉ ነገር አደረግህብን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሥራውን በቅርብ ሆነው የሚቈጣጠሩት እስራኤላውያን ኀላፊዎች ፈርዖን ፊት ቀርበው እንዲህ ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ፤ “እኛን ባሮችህን እንደዚህ የምታደርገን ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ ብለው ጮሁ፦ “ለምን አገልጋዮችህን እንዲህ ታደርጋለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ “ለምን በአገልጋዮችህ እንዲህ ታደርጋለህ? ገለባ አይሰጡአቸውም፤ ጡቡንም ሥሩ ይሉአቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን መጡ፤ “ለምን በባሪያዎችህ እንዲህ ታደርጋለህ? |
ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ።
እነዚህም ጨካኞች የሆኑት ግብጻውያን አሠሪዎች፥ የእስራኤላውያን ሠራተኞችን አለቆች “ቀድሞ ትሠሩት የነበረውን ያኽል ጡብ ሠርታችሁ የማታስረክቡት ስለምንድነው?” እያሉ ይገርፉአቸው ነበር።
ምንም ገለባ ሳይሰጠን ጡብ እንድንሠራ ታዘናል፤ ከዚህም ጋር እነሆ፥ እየተገረፍን ነው፤ ስሕተቱ ግን የገዛ ሕዝብህ ነው እንጂ የእኛ አይደለም” ሲሉ አቤቱታቸውን አቀረቡ።