ዘፀአት 40:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጋረጃውንም በድንኳኑ መግቢያ ደጃፍ ላይ ሰቀለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም መጋረጃውን በማደሪያው ድንኳን መግቢያ ላይ ሰቀለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጋረጃውን በማደሪያው መግቢያ ፊት ሰቀለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔር እንደ አዘዘው በድንኳኑ ደጅ ፊት መጋረጃውን ዘረጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በማደሪያው ደጃፍ ፊት መጋረጃውን ዘረጋ። |
እዚያም በድንኳኑ መግቢያ ፊት ለፊት የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ አኖረ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቊርባን እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእርሱ ላይ አቀረበ፤