መጋረጃውንም በድንኳኑ ጣራ ላይ በተርታ በተደረደሩት መያዣዎች ሥር ታንጠለጥለዋለህ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች የያዘውንም የቃል ኪዳን ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ በኩል ታኖረዋለህ፤ በዚህ ዐይነት መጋረጃው ቅድስት የተባለውን ስፍራ ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል፤
ዘፀአት 40:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታቦቱንም ወደ ድንኳኑ ውስጥ አስገባውና የሚከለልበትን መጋረጃ ሰቀለ፤ በዚህም ዐይነት ልክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ታቦቱን ሸፈነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ታቦቱን ወደ ማደሪያው ድንኳን አስገብቶ መከለያ መጋረጃውን ሰቀለ፤ የምስክሩንም ታቦት ጋረደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ታቦቱን ወደ ማደሪያው አስገባ፥ የሚሸፍነውን መጋረጃ አድርጎ የምስክሩን ታቦት ሸፈነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታቦቷንም ወደ ድንኳኑ አገባ፥ የሚሸፍነውንም መጋረጃ አድርጎ የምስክሩን ታቦት ሸፈነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታቦቱን ወደ ማደሪያው አገባ፥ የሚሸፍነውንም መጋረጃ አድርጎ የምስክሩን ታቦት ሸፈነ። |
መጋረጃውንም በድንኳኑ ጣራ ላይ በተርታ በተደረደሩት መያዣዎች ሥር ታንጠለጥለዋለህ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች የያዘውንም የቃል ኪዳን ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ በኩል ታኖረዋለህ፤ በዚህ ዐይነት መጋረጃው ቅድስት የተባለውን ስፍራ ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል፤