በታችኛው ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ የተሠሩ የሮማን ፍሬ ቅርጽ አድርግበት፤ በፍሬዎቹ መካከል ጣልቃ የሚገቡ ከወርቅ የተሠሩ ትናንሽ ቃጭሎች አድርግበት።
ዘፀአት 39:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት መርገፎቹ የሮማን ፍሬ፥ በልብሱ ግርጌ ዙሪያ አከታትለው አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአገልግሎት ይለበሱ ዘንድ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ላይ ተሰባጥረው ይገኙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ለማገልገል በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኩራና ሮማን፥ ሻኩራና ሮማን አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኵራንና ሮማንን፥ ሻኩራንና ሮማንን እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለማገልገል አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኵራንና ሮማንን፥ ሻኵራንና ሮማንን ለማገልገል አደረጉ። |
በታችኛው ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ የተሠሩ የሮማን ፍሬ ቅርጽ አድርግበት፤ በፍሬዎቹ መካከል ጣልቃ የሚገቡ ከወርቅ የተሠሩ ትናንሽ ቃጭሎች አድርግበት።
ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ያማሩ ናቸው፤ ስትነጋገሪም እጅግ ደስ ያሰኛሉ፤ ሁለቱ ጒንጮችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ ለሁለት የተከፈለ የሮማን ፍንካች ይመስላሉ።
እነሆ፥ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት ትሠቃይ የነበረች አንዲት ሴት፥ በዚያን ጊዜ ከኢየሱስ በስተኋላ መጥታ የልብሱን ጫፍ በእጅዋ ነካች።