ዘፀአት 39:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተጨማሪም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተው በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው የደረት ኪስ ሁለት የውስጥ ጫፎች ላይ አደረጉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከኤፉዱ ቀጥሎ ካሉት ከሌሎቹ ሁለት የደረት ኪስ ጐኖች ጋራ ከውስጠኛው ጠርዝ ላይ አያያዟቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት የወርቅ ቀለበቶችንም ሠሩ፥ እነርሱንም በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረቱ ኪስ በሁለት ጫፎቹ ላይ አደረጉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱንም የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፤ እነርሱንም ከልብሰ መትከፉ ፊት ለፊት ባለው በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ጫፎች ላይ አደረጓቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱንም የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፥ እነርሱንም በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረቱ ኪስ በሁለት ጫፎቹ ላይ አደረጉአቸው። |
ሌሎቹንም የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች ከሁለቱ ፈርጦች ጋር እንዲገናኙ አደረጉ፤ በዚህም ዐይነት በትከሻ ላይ በሚወርዱት በኤፉድ ማንገቻ ጥብጣቦች ፊት ለፊት እንዲያያዙ አደረጉ።
ቀጥሎም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተው በትከሻ ላይ በፊት በኩል ከሚወርዱት ከሁለቱ የኤፉዱ ጥብጣቦች ጋር ከታች በኩል አያያዙአቸው፤ እነርሱም የተያያዙት በብልኀት ከተጠለፈው ቀበቶ በላይ ከመጋጠሚያው አጠገብ ነበር።