ዘፀአት 39:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱንም የወርቅ ድሪዎች ከቀለበቶቹ ጋር እንዲያያዙ አደረጉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱን የወርቅ ድሪዎች በደረት ኪሱ ጐንና ጐን ካሉት ቀለበቶች ጋራ አያያዟቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱንም የተጐነጐኑትን የወርቅ ድሪዎች በደረቱ ኪስ ጫፎች ባሉት በሁለቱ ቀለበቶች አስገቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱንም የተጐነጐኑትን የወርቅ ድሪዎች በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ወገኖች ወዳሉት ወደ ሁለቱ ቀለበቶች አገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱንም የተጐነጐኑትን የወርቅ ድሪዎች በደረቱ ኪስ ወገኖች ወዳሉት ወደ ሁለቱ ቀለበቶች አገቡ። |
ሌሎቹንም የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች ከሁለቱ ፈርጦች ጋር እንዲገናኙ አደረጉ፤ በዚህም ዐይነት በትከሻ ላይ በሚወርዱት በኤፉድ ማንገቻ ጥብጣቦች ፊት ለፊት እንዲያያዙ አደረጉ።