ዘፀአት 39:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራተኛው ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድና ኢያስጲድ፤ እነዚህ ሁሉ በወርቅ ፈርጥ ላይ የተቀመጡ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያሰጲድ ነበረ፤ በወርቅ ፈርጥ ላይ ተደርገው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድና ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ተደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራተኛውም ተራ ወርቃማ ድንጋይ፥ ቢረሌ፥ ሶም፤ ዙሪያውም በወርቅ ፈርጥ ተደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራተኛውም ተራ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ተደረጉ። |
የምችለውን ያኽል፥ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሚሆኑትን ዕቃዎች ወርቅ ለወርቅ ሥራ፥ ብር ለብር ሥራ፥ ነሐስ ለነሐስ ሥራ፥ ብረት ለብረት ሥራ፥ እንጨት ለእንጨት ሥራ መርግድና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው በፈርጥ የሚገቡ ድንጋዮች፥ የከበረ ድንጋይና በየዐይነቱ ብዙ ዕብነ በረድ አዘጋጅቼአለሁ።
በሁለቱ ድንጋዮች ላይ የዐሥራ ሁለቱን የያዕቆብ ልጆች ስሞች ለመቅረጽም ችሎታ ያለው ብልኅ ሰው አግኝ፤ ድንጋዮቹንም ከወርቅ በተሠራ ፈርጥ ላይ አኑራቸው።
የከበሩት ድንጋዮች ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ነገድ በመወከል እንዲታሰቡ በእያንዳንዱ ድንጋይ ላይ ከዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ስሞች አንዱ ስም ተቀርጾበታል።
አራቱም መንኰራኲሮች ተመሳሳይ ነበሩ፤ እያንዳንዱም እንደ ከበረ ዕንቊ ያንጸባርቅ ነበር፤ እንዲሁም እያንዳንዱ አንዱ መንኰራኲር በሌላው መንኰራኲር ውስጥ የሚተላለፍ ይመስል ነበር።
አምስተኛው ሰርዶንክስ፥ ስድስተኛው ሰርድዮን፥ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፥ ስምንተኛው ቢረሌ፥ ዘጠነኛው ወራውሬ፤ ዐሥረኛው ክርስጵራስስ፥ ዐሥራ አንደኛው ያክንት፥ ዐሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበረ።