ዘፀአት 38:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብሩም ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚሆነው ለተቀደሰው ድንኳንና ለመጋረጃዎች መቆሚያ የሚሆኑ አንድ መቶ እግሮች የተሠሩበት ነበር፤ ይኸውም ለእያንዳንዱ እግር ሠላሳ አራት ኪሎ ግራም ተመድቦለት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ መቶ የብር መክሊቶች የመቅደሱንና የመጋረጃዎቹን መቆሚያዎች ለመሥራት አገልግሎት ላይ ውለው ነበር፤ ይኸውም ከአንድ መቶ መክሊቶች አንድ መቶ መቆሚያዎች ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ መቆሚያ አንድ መክሊት ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቶው የብር መክሊት የመቅደሱንና የመጋረጃውን እግሮች ለመሥራት ነበረ፤ ከመቶ መክሊት መቶ እግሮች ተሠሩ ይኸውም ለአንድ እግር አንድ መክሊት ማለት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቶውም የብር መክሊት ለድንኳኑ ምሰሶዎች እግሮችና ለመጋረጃው ምሰሶዎች እግሮች ተደረገ፤ መቶውም መክሊት ለመቶ እግሮች፤ ለአንድ እግርም አንድ መክሊት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቶውም የብር መክሊት የመቅደሱንና የመጋረጃውን እግሮች ለመሥራት ነበረ፤ ከመቶውም መክሊት መቶ እግሮች አደረገ፤ ለአንድ እግርም አንድ መክሊት ነበረ። |
ይህም በሕዝብ ቈጠራ ጊዜ የተመዘገቡት ሰዎች እያንዳንዳቸው በይፋ በታወቀው ሚዛን ልክ የከፈሉትን ድርሻ ጠቅላላ ድምር የሚያኽል ነበር፤ በሕዝብ ቈጠራ የተመዘገቡትም ኻያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ የሆኑት ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ወንዶች ነበሩ።