ዘፀአት 37:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከክፈፉም ሥር ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አደረገ፤ በሁለቱም ጐን ግራና ቀኝ አኖራቸው፤ እነርሱም የዕጣን መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉ መሎጊያዎች የሚሾልኩባቸው ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሸክም የሚሆኑትን መሎጊያዎች ለመያዝ ትይዩ የሆኑ ከክፈፉ ሥር ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አደረገበት፥ በሁለቱም ጎን በሁለቱም ማዕዘን አደረጋቸው፥ ለመሸከምም የመሎጊያዎቹ ስፍራ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አደረገበት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱም ጎን አደረጋቸው፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች መግቢያ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አደረገበት፥ በዚህና በዚያ በሁለቱም ጎን አደረጋቸው፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች ስፍራ ነበሩ። |