ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለዘብ ጠባቂዎችና ለጦር መኰንኖች “ገብታችሁ እነዚህን ሁሉ ግደሉ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሰይፍ ሰይፋቸውን በመምዘዝ ገብተው ሁሉንም ገደሉ፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጐተቱ ወደ ውጪ አወጡት፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገብተው፥
ዘፀአት 32:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አላቸው፦ “እያንዳንዳችሁ ሰይፋችሁን መዛችሁ ከዚህ በር እስከ ወዲያኛው በር ድረስ በሰፈሩ ውስጥ በመመላለስ ያለ ምንም ምሕረት ወንድሞቻችሁን፥ ወዳጆቻችሁንና ጐረቤቶቻችሁን እንድትገድሉ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አዞአችኋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘እያንዳንዱ ሰው በወገቡ ላይ ሰይፍ ይታጠቅ፤ በሰፈር ውስጥ ከዳር እዳር እየተመላለሰ እያንዳንዱ ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል’ ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዱ ሰው ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፥ በሰፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ወዲህ ወዲያ ተመላለሱ፥ ሰው ሁሉ ወንድሙን፥ ሰው ሁሉ ወዳጁን፥ ሰው ሁሉ ጎረቤቱን ይግደል’” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፤ ሂዱና በሰፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፤ እያንዳንዱም ወንድሙን፥ እያንዳንዱም ጎረቤቱን፥ እያንዳንዱም የቅርቡን ይግደል” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእናንተ ሰው ሁሉ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፥ በሰፈሩም ውስጥ በዚህና በዚያ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፥ የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም ይግደል አላቸው። |
ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለዘብ ጠባቂዎችና ለጦር መኰንኖች “ገብታችሁ እነዚህን ሁሉ ግደሉ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሰይፍ ሰይፋቸውን በመምዘዝ ገብተው ሁሉንም ገደሉ፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጐተቱ ወደ ውጪ አወጡት፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገብተው፥
ስለዚህ በሰፈሩ ደጃፍ ቆሞ “የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ!” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ፤ ሌዋውያንም ሁሉ በዙሪያው ተሰበሰቡ፤
ሙሴም ሌዋውያንን እንዲህ አለ፤ “ዛሬ ልጆቻችሁንና ወንድሞቻችሁን በመግደል እግዚአብሔርን የምታገለግሉ ካህናት ሆናችሁ ራሳችሁን ቀድሳችኋል፤ እግዚአብሔርም በረከቱን ሰጥቶአችኋል።”
እንደገናም እግዚአብሔር ሌሎቹን ሰዎች እንዲህ ሲላቸው ሰማሁ፦ “በሉ እናንተም እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ ውስጥ በመዘዋወር ሁሉን ግደሉ፤ ለማንም በመራራት ምሕረት አታድርጉ።
“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም።
“በቅርብም ሆነ በሩቅ ካሉት፥ ከአንዱ የምድር ዳርቻ በአካባቢህ ካሉ ከአሕዛብ አማልክት አንተ ወይም አባቶችህ የማታውቁትን አንዱን እናምልክ በማለት ሌላ እንኳ ቀርቶ የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ በምሥጢር ይገፋፋህ ይሆናል።