ዘፀአት 32:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከወርቅ የተሠሩ ጌጣጌጦቻቸውን አውልቀው እንዲያመጡልኝ ነገርኳቸው፤ እነርሱም ያላቸውን ጌጣጌጥ ሁሉ አመጡልኝ፤ ጌጣጌጦቹንም ወደ እሳት ውስጥ በጣልኳቸው ጊዜ ይህ የጥጃ ምስል ወጣ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ ‘ማንኛውም ዐይነት የወርቅ ጌጣጌጥ ያለው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው፤ ከዚያም ወርቁን ሰጡኝ፤ ወደ እሳቱ ጣልሁት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ ‘ከእናንተ ወርቅ ያለው ሰው ሁሉ ሰብሮ ያምጣልኝ’ አልኋቸው፤ እነርሱም ሰጡኝ፥ በእሳት ላይ ጣልሁት፥ ይህም ጥጃ ወጣ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ከእናንተ ወርቅ ያለው ሰው ያምጣልኝ አልኋቸው፤ ሰጡኝም፤ በእሳትም ላይ ጣልሁት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ ከእናንተ ወርቅ ያለው ሰው ከእርሱ ሰብሮ ያምጣልኝ አልኋቸው፤ ሰጡኝም፤ በእሳትም ላይ ጣልሁት፥ ይህም ጥጃ ወጣ። |
እርሱም የወርቅ ጒትቻውን ሁሉ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፤ የቀለጠውንም ወርቅ በቅርጽ መሥሪያ ውስጥ አግብቶ የወርቅ ጥጃ አድርጎ ሠራው። እነርሱም “እስራኤል ሆይ! ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላካችን ይህ ነው!” አሉ።