እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊትም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ፤
ዘፀአት 31:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱም ጋር እንዲሠራ ከዳን ነገድ የአሒሳማክን ልጅ ኦሆሊአብን መርጬአለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን ነገር ሁሉ እንዲሠሩ ሌሎችም የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ታላቅ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጌአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተጨማሪም ከዳን ነገድ የሆነውን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን እንዲረዳው መርጬዋለሁ። “እንዲሁም ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ ለእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ብልኀትን ሰጥቻቸዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም እነሆ ከእርሱ ጋር ከዳን ነገድ የሆነውን የአሒሳማክን ልጅ ኤልያብን ሰጥቼዋለሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ እንዲያደርጉ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ላይ ጥበብን አኑሬአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ዕውቅትን ሰጠሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እነሆ ከእርሱ ጋር ከዳን ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ጥበብን አኖርሁ። |
እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊትም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ፤
እኔ ልዩ ችሎታ እንዲኖራቸው ያደረግኋቸውን የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችን ጠርተህ ለአሮን ልብስ እንዲሠሩለት ንገራቸው፤ በዚህ ዐይነት አሮን ካህን በመሆን ያገለግለኝ ዘንድ ለእኔ የተለየ ይሆናል።
በአንጥረኛ፥ በፕላን አውጪ ባለሞያ፥ ጥሩ በፍታ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ቀለም የተነከረ ከፈይ ሌላውንም የልብስ ሥራ በሚያከናውኑ ሸማኔዎች የተሠራውን ነገር ሁሉ ለማስጌጥ የሚችሉበትን ብልኀት ሰጥቶአቸዋል፤ እነርሱ ማናቸውንም የጥበብ ሥራ ለመሥራትና በብልኀት የሚሠራውንም ሁሉ ዕቅድ ለማውጣት የሚችሉ ናቸው።
ሥራውን ከሚያከናውኑት መካከል እጅግ ጥበበኞች የነበሩት የተቀደሰውን ድንኳን ሠሩ፤ እነርሱም ድንኳኑን ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተሉ፥ የኪሩቤል ሥዕል ከተጠለፈባቸው ዐሥር የበፍታ መጋረጃዎች ሠሩት።
ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሒሳማክ ልጅ አሆሊአብም አንጥረኛ፥ ፕላን አውጪ ባለሞያ፥ እንዲሁም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ እየጠለፈ ጥሩ በፍታ የሚሠራ ሸማኔ ነበር።
ከዚህ በኋላ ጌታ፥ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ እርሱ ሊሄድበት ወደአሰበውም ከተማና ቦታ ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው።
ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።