በሌላ በኩል ያሉትንም የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች ከሁለቱ ፈርጦች ጋር አገናኛቸው፤ በዚህም ዐይነት ከፊት ለፊት በኩል በትከሻ ላይ ከሚወርዱት ከኤፉዱ ማንገቻዎች ጋር ታያይዛቸዋለህ፤
ዘፀአት 28:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱ ወገን አንድ እንዲሆን በሁለቱ ትከሻ ላይ የሚጋጠም የጥብጣብ ዐይነት ማንገቻ ይኑር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መተሳሰር እንዲችል ሆኖ፣ ዳርና ዳር ከሚገኙት ከሁለቱ ጐኖች ጋራ የተያያዙ ሁለት የትከሻ ንጣዮች ይኑሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱ ወገን አንድ ሆኖ እንዲጋጠም በሁለቱ ትከሻ ላይ የሚጋጠም ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱ ወገን አንድ እንዲሆን በሁለቱ ጫንቃ ላይ የሚጋጠም ጨርቅ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱ ወገን አንድ እንዲሆን በሁለቱ ጫንቃ ላይ የሚጋጠም ጨርቅ ይሁን። |
በሌላ በኩል ያሉትንም የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች ከሁለቱ ፈርጦች ጋር አገናኛቸው፤ በዚህም ዐይነት ከፊት ለፊት በኩል በትከሻ ላይ ከሚወርዱት ከኤፉዱ ማንገቻዎች ጋር ታያይዛቸዋለህ፤
ሌሎቹንም የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች ከሁለቱ ፈርጦች ጋር እንዲገናኙ አደረጉ፤ በዚህም ዐይነት በትከሻ ላይ በሚወርዱት በኤፉድ ማንገቻ ጥብጣቦች ፊት ለፊት እንዲያያዙ አደረጉ።