አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ዐይናችንን አበራህ፤ እነሆ፥ አሁን ደግሞ ለጥቂት ጊዜ በፊትህ ሞገስን አግኝተን ከእኛ ጥቂቶቹ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥተው በዚህች ቅድስት ምድር በሰላም ይኖሩ ዘንድ ፈቅደሃል፤ ምንም እንኳ በባርነት አገዛዝ ሥር ብንወድቅም እነሆ አዲስ ሕይወት ሰጥተኸናል።
ዘፀአት 27:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንኳኑ ውስጥ የሚገኙት ለማናቸውም ጥቅም የሚውሉ የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎች ሁሉ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥቅማቸው ምንም ዐይነት ይሁን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ከንሓስ የተሠሩ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፥ ካስማዎቹ ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ፥ የነሐስ ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለማገልገል ሁሉ የድንኳን ዕቃ ሁሉ፥ አውታሮቹ ካስማዎቹም ሁሉ፤ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ የናስ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለማገልገል ሁሉ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፥ ካስማዎቹም ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ፥ የናስ ይሁኑ። |
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ዐይናችንን አበራህ፤ እነሆ፥ አሁን ደግሞ ለጥቂት ጊዜ በፊትህ ሞገስን አግኝተን ከእኛ ጥቂቶቹ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥተው በዚህች ቅድስት ምድር በሰላም ይኖሩ ዘንድ ፈቅደሃል፤ ምንም እንኳ በባርነት አገዛዝ ሥር ብንወድቅም እነሆ አዲስ ሕይወት ሰጥተኸናል።
የድንኳኑ አደባባይ ርዝመቱ አርባ አራት ሜትር የጐኑ ስፋት ኻያ ሁለት ሜትር፥ ከፍታውም ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ይሁን፤ መጋረጃዎቹ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ ሆነው የነሐስ እግሮች ይኑሩአቸው።
ዐመድ የሚጠራቀምባቸውን ድስቶችን፥ የእሳት መጫሪያዎችን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን አዘጋጅ፤ ሁሉም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።
በዙሪያ ያለው የአደባባይ አጥርና ወደ አደባባዩ የሚያስገባው ደጃፍ የሚቆሙባቸውን እግሮች፥ እንዲሁም የድንኳኑና በዙሪያው ያለውን የአደባባይ አጥር ካስማዎችን ሁሉ ሠራ።
ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ የሚሆኑት መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹና የሚቆሙባቸው እግሮች፥ ለአደባባዩ መግቢያ የተሠራው መጋረጃና አውታሮቹ፥ ድንኳኑ የሚተከልባቸው ካስማዎች፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙ የመገልገያ ዕቃዎች፥
የጠቢባን ንግግር፥ እረኛ የከብቶቹን መንጋ እንደሚነዳበት ጫፉ እንደ ሾለ በትር ነው፤ በአንድነት የተከማቹ ምሳሌዎች ጠልቀው እንደሚገቡ ምስማሮች ናቸው፤ እነርሱም ከሁላችን ጠባቂ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸው።
የታወቁ የሃይማኖት በዓላትን የምናከብርባትን የጽዮንን ከተማ ተመልከቱ፤ በሰላም ትኖሩባት ዘንድ ምቹ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን እዩ! ካስማዎቹ ከቶ እንደማይነቀሉ፥ ገመዶቹም እንደማይበጠሱና ከስፍራው እንደማይንቀሳቀስ ድንኳን ትሆናለች።
እንዲሁም በድንኳኑ ዙሪያ የሚገኘውን አደባባይ ምሰሶችን፥ እግሮቻቸውን፥ ካስማዎችን፥ አውታሮችንና ለእነዚህ ሁሉ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ነው፤ እያንዳንዱም መሸከም ያለበትን ዕቃ በየስሙ ትመድብለታለህ።