ዘፀአት 25:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ልክ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ እንዳሳየሁህ ሁሉ፥ እንደ ድንኳኑ ምሳሌ፥ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተራራው እንዳሳየሁህ ሁሉ፥ እንደ ማደሪያው ምሳሌ፥ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ ለእኔ ትሠራለህ፤ እንዲሁ ትሠራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ እንደማሳይህ ሁሉ፥ እንደ ማደሪያው ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት። |
በመቅደሱ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑአቸው፤ የለፋ ስስ ቊርበት ደርበውም በመሸከሚያው ተራዳ ላይ ያኑሩአቸው።
እነዚህ ካህናት የሚያገለግሉበት ድንኳን በሰማይ ለሚገኘው ምሳሌና ጥላ ብቻ ነው፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኒቱን በሚሠራበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር “በተራራው ላይ እንደ ተገለጠልህ ዐይነት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ አድርግ” ብሎ ባዘዘው መሠረት ነው።
ሁለት ክፍሎች ያሉአት ድንኳን ተዘጋጅታ ነበር። መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት የነበረባት መጀመሪያይቱ ክፍል “ቅድስት” ትባል ነበር።