ዘፀአት 25:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መረግድ፥ (ቅጠልያ ዕንቊ) በሊቀ ካህናቱ ኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚደረግ ፈርጥ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቍዎች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መረግድ፥ ለኤፉድና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መረግድም፥ ለልብሰ እንግድዓና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መረግድም፥ ለኤፉድና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ። |
በዐይነት የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ የደረት ኪስ፥ ኤፉድ፥ ቀሚስ፥ በጥልፍ ያጌጠ ሸሚዝ፥ ጥምጥምና መታጠቂያ፤ ወንድምህ አሮንና ልጆቹ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ እነዚህን የተቀደሱ ልብሶች ይሥሩላቸው።