ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ሚስቶች የሚሆኑ ከእነዚያ ወገኖች አግብተዋል፤ አጋብተዋልም፤ ቅዱሱን ዘር ከሌሎች ከአካባቢው አሕዛብ ጋር ቀላቅለዋል፤ በዚህ እምነተ ቢስ በሆነ ተግባር መሪዎቹና ባለ ሥልጣኖቹ ግንባር ቀደም ሆነዋል።”
ዘፀአት 22:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ ለእኔ የተለያችሁ ሰዎች ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ አውሬ በሜዳ የገደለውን የማንኛውንም እንስሳ ሥጋ አትብሉ፤ ለውሾች ጣሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤ ስለዚህ አውሬ የዘነጠለውን የእንስሳ ሥጋ አትብሉ፤ ለውሾች ስጡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ አውሬ የገደለውን ሥጋ ለውሻ ጣሉት እንጂ አትብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ በምድረ በዳ አውሬ የቧጨረውን ሥጋ ለውሻ ጣሉት እንጂ አትብሉት። |
ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ሚስቶች የሚሆኑ ከእነዚያ ወገኖች አግብተዋል፤ አጋብተዋልም፤ ቅዱሱን ዘር ከሌሎች ከአካባቢው አሕዛብ ጋር ቀላቅለዋል፤ በዚህ እምነተ ቢስ በሆነ ተግባር መሪዎቹና ባለ ሥልጣኖቹ ግንባር ቀደም ሆነዋል።”
እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”
ስለዚህም ንጹሓን በሆኑትና ንጹሓን ባልሆኑት እንስሶችና ወፎች መካከል ልዩነት አድርጉ፤ እኔ ርኩሳን ናቸው ብዬ ለይቼ ባስታወቅኋችሁና በምድር ላይ በሚገኙ እንስሶች፥ ወፎችና ሌሎችም ነገሮች ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ፤
ይልቅስ ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብን አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ሳይታረድና ደሙም ሳይፈስ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምንም አትብሉ’ ብለን እንጻፍላቸው።
“ሞቶ የተገኘውን እንስሳ አትብላ፤ በመካከልህ የሚኖሩ የውጪ አገር ሰዎች እንዲመገቡት ፍቀድላቸው፤ ወይም ለውጪ አገር ሰዎች በዋጋ ልትሸጥላቸው ትችላለህ። አንተ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየህ ሕዝብ ነህ። “የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።