የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።
ዘፀአት 21:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሬው ወንድ ወይም ሴት ባሪያ ወግቶ ቢገድል የበሬው ባለቤት ለባሪያው ጌታ ሠላሳ ብር ይክፈለው፤ በሬውም በድንጋይ ተወግሮ ይሙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ በሬ ወንድ ወይም ሴት ባሪያን ቢወጋ ባለቤቱ ሠላሳ የብር ሰቅል ለባሪያው ጌታ መክፈል አለበት፤ በሬውም በድንጋይ ይወገር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሬው ወንድ ባርያ ወይም ሴት ባርያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታው ይስጥ፥ በሬው ግን ይወገር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታቸው ይስጥ፤ በሬውም ይወገር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታቸው ይስጥ፥ በሬውም ይወገር። |
የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።