እግዚአብሔር ግን “ማንም አይነካህም፤ አንተን የሚገድል ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል” አለው። ስለዚህ እግዚአብሔር ቃየልን ማንም ቢያገኘው እንዳይገድለው የሚያስጠነቅቅ ልዩ ምልክት አደረገለት።
ዘፀአት 21:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ወንድም ሆነ ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታና ወዲያው ቢሞትበት መቀጣት ይገባዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው ወንድ ወይም ሴት ባሪያውን በዱላ ቢመታና ባሪያውም በዚህ የተነሣ ቢሞት መቀጣት አለበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰው ወንድ ባርያውን ወይም ሴት ባርያውን በበትር ቢመታ፥ በእጁም ቢሞትበት፥ ያው ቅጣት ይቀጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰውም ወንድ ባሪያውን ወይም ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታ፥ በእጁ ቢሞትበትም፥ ፈጽሞ ይቀጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ወንድ ባሪያውን ወይም ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታ፥ ቢሞትበትም፥ ፈጽሞ ይቀጣ። |
እግዚአብሔር ግን “ማንም አይነካህም፤ አንተን የሚገድል ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል” አለው። ስለዚህ እግዚአብሔር ቃየልን ማንም ቢያገኘው እንዳይገድለው የሚያስጠነቅቅ ልዩ ምልክት አደረገለት።
በኋላም ተነሥቶ በትር እየተመረኰዘ መራመድ ቢቀጥል፤ ስለ ባከነበት ጊዜ የመታው ሰው ካሣ ይክፈለው፤ በደንብ እስከሚድንም ድረስ ተገቢውን እንክብካቤ ያድርግለት።
ባለሥልጣን ለአንተ መልካም እንዲያደርግ የተሾመ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፤ ባለሥልጣን ሰይፍ የታጠቀው በከንቱ ስላልሆነ ክፉ አድራጊ ከሆንክ ባለሥልጣንን ፍራ፤ እርሱ ክፉ አድራጊዎችን በመቅጣትና የእግዚአብሔርን በቀል በማሳየት እግዚአብሔርን ያገለግላል።
በእንደዚህ ያለው ክፉ ነገር ላይ ሁሉ ምንም ዐይነት ምሕረት አይኑርህ፤ የቅጣቱም አፈጻጸም ሕይወት ያጠፋ፥ ሕይወቱ እንዲጠፋ፤ ዐይን ያጠፋ፥ ዐይኑ እንዲጠፋ፤ ጥርስ ያወለቀ፥ ጥርሱ እንዲወልቅ፤ እጅ የቈረጠ፥ እጁ እንዲቈረጥ፤ እግርም የሰበረ፥ እግሩ እንዲሰበር በማድረግ ይሁን።