ዘፀአት 19:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሦስተኛው ቀን ማለዳ የነጐድጓድ ድምፅ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭልጭታና ጥቅጥቅ ያለ ደመና በተራራው ላይ ታየ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የእምቢልታ ድምፅ ተሰማ። ሰዎቹም በሰፈሩበት ቦታ ፈርተው ተንቀጠቀጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛውም ቀን ጧት ከባድ ደመና በተራራው ላይ ሆኖ ነጐድጓድና መብረቅ እንዲሁም ታላቅ የቀንደ መለከት ድምፅ ነበር፤ በሰፈሩ ያሉት ሁሉ ተንቀጠቀጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጐድጓድና መብረቅ፥ ከባድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጎድጓድና መብረቅ ከባድም ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን “እኔ ግዙፍ በሆነ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ስለዚህም ሕዝቡ እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር በመስማት ከአሁን ጀምሮ አንተ የምትለውን ሁሉ ያምናሉ።” ሙሴም ሕዝቡ የሰጠውን መልስ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤
ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤
ስለዚህ ሙሴ በትሩን አንሥቶ ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና በረዶ መብረቅም ወደ ምድር አወረደ፤ በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር በግብጽ ምድር ላይ በረዶን አዘነበ።
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ታዲያ ስለምን አታከብሩኝም? በፊቴስ ለምን አትንቀጠቀጡም፤ አሸዋን ውሃ አልፎት እንዳይሄድ ለዘለዓለሙ የባሕር ወሰን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ ባሕር የቱንም ያኽል ቢናወጥ፥ ማዕበል፥ ሞገዱም ቢያስገመግም፥ ወሰን የሆነውን የአሸዋ ግድብ አልፎ መሄድ አይችልም።
እግዚአብሔር ታጋሽና ኀያል ነው፤ ነገር ግን በደለኛውን ሳይቀጣው አያልፍም፤ መንገዱ በዐውሎ ነፋስና በሞገድ ውስጥ ነው፤ ሰው ሲራመድ ትቢያን እንደሚያስነሣ፥ የእግዚአብሔርም መገለጥ ደመናን ያስከትላል።
ታላቅ የእምቢልታ ድምፅ የሚያሰሙ መላእክቱን ይልካል፤ እነርሱ በአራቱም የዓለም ማዕዘኖች ሄደው ከሰማይ ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ ያሉትን የእርሱን ምርጥ ሰዎች ይሰበስባሉ።”
እናንተ እሳቱን በመፍራት ወደ ተራራው መውጣት ስለ ፈራችሁ እኔ በዚያን ጊዜ እርሱ የሚለውን ሁሉ ልነግራችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ቆምኩ፤ “እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤
በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።
ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እነሆ በሰማይ የተከፈተ በር ነበር፤ በመጀመሪያ ሰምቼው የነበረው እንደ እምቢልታ ያለው ድምፅ እንዲህ አለ፦ “ና ወደዚህ ውጣ፤ ወደፊት መሆን የሚገባቸውን ነገሮች አሳይሃለሁ፤”
ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጡ ነበር፤ በዙፋኑ ፊት የሚበሩ ሰባት ችቦዎች ነበሩ፤ እነርሱ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።