ዘፀአት 13:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀንና ሌሊት መጓዝ ይችሉ ዘንድ፥ እግዚአብሔር ቀን በደመና ዐምድ፥ ሌሊት ደግሞ ብርሃን በሚሰጥ በእሳት ዐምድ ይመራቸው ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በቀንም ሆነ በሌሊት መጓዝ ይችሉ ዘንድ፣ እግዚአብሔር በቀን በመንገዳቸው ሊመራቸው በደመና ዓምድ፣ በሌሊት ደግሞ ብርሃን ሊሰጣቸው በእሳት ዐምድ በፊታቸው ይሄድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀንና በሌሊትም እንዲጓዙ፥ ጌታ ቀን በደመና ዓምድ መንገድ ሊመራቸው፥ ሌሊት ደግሞ በእሳት ዓምድ ሊያበራላቸው ከፊታቸው ይሄድ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በዐምደ ደመና፥ ሌሊትም በዐምደ እሳት ይመራቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ፥ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ። |
ምሕረትህም ታላቅ በመሆኑ በዚያ ምድረ በዳ ይጠፉ ዘንድ አልተውካቸውም፤ ነገር ግን የደመናው ዐምድ በቀን ይመራቸው ነበር፤ የእሳቱ ዐምድ በሌሊት ያበራላቸው ነበር።
ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “እስቲ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ የዐመፅ ሤራ ማቀዳችሁ ግልጥ ስለ ሆነ ሴቶቻችሁንና ልጆቻችሁን ይዛችሁ እንድትሄዱ አልፈቅድላችሁም!
ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እዚያ ብዙ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ በአንድነት በመሰብሰብ አሮንን ከበው “ያ ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅም፤ ስለዚህ በፊት በፊታችን እየሄዱ የሚመሩን አማልክትን ሥራልን” አሉት።
የሆነውን ሁሉ በዚህ ምድር ለሚኖሩት ሕዝቦች ይነግራሉ፤ እነዚህ ሕዝቦች አንተ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆንህንና ደመናህ በላያችን በረበበ ጊዜ በግልጥ እንደምትታይ፥ ቀን በደመና ዐምድ፥ ሌሊት በእሳት ዐምድ እፊት እፊታችን እየሄድክ እንደምትመራን ከሰሙ ቈይተዋል።