ዘፀአት 12:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከሚነጋም ድረስ ከሥጋው ምንም ነገር አታስተርፉ፤ የተረፈ ነገር ቢኖር ሁሉንም በእሳት አቃጥሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሥጋው ተርፎ አይደር፤ ያደረ ቢኖር ግን በእሳት ይቃጠል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ እስከ ጥዋት የቀረውንም በእሳት አቃጥሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ አጥንቱንም ከእርሱ አትስበሩ፤ ከእርሱም እስከ ጥዋት የተረፈ ቢኖር በእሳት አቃጥሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ እስከ ጥዋት የቀረውን በእሳት አቃጥሉት። |
“እንስሳ በምትሠዉልኝ ጊዜ እርሾ የነካው እንጀራ መባ አድርጋችሁ አታቅርቡ፤ በእነዚህ በዓላት የሚሠዉት እንስሶች ስብ ለሚቀጥለው ቀን አይትረፍ።
“ለእኔ የእንስሶች መሥዋዕት በምትሠዉበት ጊዜ ደሙን እርሾ ካለበት ኅብስት ጋር አታቅርቡልኝ ለፋሲካ በዓል ከታረደው እንስሳ ምንም ሥጋ እስከ ማግስቱ ጠዋት ድረስ አታቈዩ።
እስከ ማግስቱ ጠዋት ድረስ ከዚያ ምግብ አስተርፈው አያሳድሩ፤ ከእንስሳውም አጥንት አንዱንም አይስበሩ፤ በተሰጣቸው የሥርዓት መመሪያ መሠረት በዓሉን ያክብሩ፤