አስቴር 1:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ንጉሡ አርጤክስስ ሱሳ በምትገኘው ቤተ መንግሥቱ ይኖር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዘመን ንጉሡ ጠረክሲስ የገዛው በሱሳ ግንብ ባለው ንጉሣዊ ዙፋኑ ሆኖ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዘመን ንጉሡ አርጤክስስ በሱሳ ግንብ በነበረው በመንግሥቱ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ሳለ፥ |
የሐካልያ ልጅ ነህምያ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በሃያኛው ዓመት ኪስሌው ተብሎ በሚጠራው ወር እኔ ነህምያ ዋና ከተማ በሆነችው በሱሳ ውስጥ ነበርኩ።
በንጉሠ ነገሥትህ ግዛት በየአገሩ ባለ ሥልጣኖችን በመሾም ውብ የሆኑትን ልጃገረዶች እየመረጡ መናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳ ውስጥ ለአንተ የተመረጡ ሴቶች መኖሪያ ወደ ሆነው ቤት እንዲያመጡአቸው ይደረግ፤ የዚህም ቤት ኀላፊ ባደረግኸው በጃንደረባው ሄጋይ ቊጥጥር ሥር ይጠበቁ፤ የቊንጅናም እንክብካቤ ይደረግላቸው።
እዚያም በሱሳ ከተማ የሚኖር መርዶክዮስ ተብሎ የሚጠራ አንድ አይሁዳዊ ነበር፤ እርሱ የያኢር ልጅ ሲሆን ከብንያም ነገድ የቂስና የሺምዒ ዘር ነበር።
በንጉሡም ትእዛዝ ዐዋጁ ሱሳ ተብላ በምትጠራው መናገሻ ከተማ በይፋ ተገልጦ እንዲታይ ተደረገ፤ ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ወደየአገሩ መልእክቱን አደረሱ፤ መናገሻ ከተማይቱ ሱሳ ታውካ ሳለች፥ ንጉሡና ሃማን በአንድነት ተቀምጠው የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።
“ሄደህ በሱሳ የሚገኙትን አይሁድ በአንድነት ሰብስብ፤ ጾም ዐውጃችሁም ለእኔ ጸልዩ፤ እስከ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም ዐይነት ምግብ አትብሉ፤ ምንም ዐይነት መጠጥ አትጠጡ፤ እኔና ደንገጡሮቼም በዚሁ ዐይነት እንቈያለን፤ ከዚህም በኋላ በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ደፍሬ ወደ ንጉሡ ዘንድ እገባለሁ፤ ይህን በማድረጌ ብሞትም ልሙት።”