“ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
መክብብ 5:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ሁሉ ራቁቱን እንደ ተወለደ ባዶ እጁን ተመልሶ ይሄዳል፤ የቱንም ያኽል በሥራ ቢደክም ይዞት የሚሄደው ነገር የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ከእናቱ ማሕፀን ዕራቍቱን ይወለዳል፤ እንደ መጣው እንዲሁ ይመለሳል። ከለፋበትም ነገር፣ አንድም እንኳ በእጁ ይዞ ሊሄድ አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ደግሞ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ነው፥ እንደመጣ እንዲሁ ይሄዳል፥ ድካሙም ለነፋስ ከሆነ ጥቅሙ ምንድነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናቱ ሆድ ራቁቱን እንደ ወጣ እንዲሁ እንደ መጣው ይመለሳል፤ ከጥረቱም በእጁ ሊወስድ የሚችለው ምንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናቱ ሆድ ራቁቱን እንደ ወጣ እንዲሁ እንደ መጣው ይመለሳል፥ ከጥረቱም በእጁ ሊወስድ የሚችለውን ምንም አያገኝም። |
“ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ የያዕቆብንም ልጆች እንደ አካሄዳቸው ይቀጣቸዋል፤ ባደረጉትም ክፉ ሥራ መጠን ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል።