ዘዳግም 33:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመሪነት ድርሻ ስለ ተቀመጠለት፥ ለራሱ የተሻለውን መሬት መረጠ፤ የሕዝብ አለቆች በተሰበሰቡ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈቃድና ሥርዓቱን ለእስራኤል ፈጸመ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ፤ የአለቃም ድርሻ ለርሱ ተጠብቆለታል። የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፈቃድና፣ በእስራኤል ላይ የበየነውን ፍርዱን ፈጸመ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፥ ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፥ የጌታንም ጽድቅ፥ ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ከሕዝቡ ገዦች ጋር የተሰበሰቡ የአለቆች ምድር እንደ ተከፈለች፥ የመጀመሪያውን ፍሬ አየ፤ እግዚአብሔርም ጽድቁን፥ ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና 2 የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፤ 2 ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፤ 2 የእግዚአብሔርንም ጽድቅ፥ 2 ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ። |
ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቈዩ፤ የጦር ልብስ ለብሰው ለውጊያ የተዘጋጁ ሰዎቻችሁ ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን ለመርዳት ግንባር ቀደም ሆነው ዮርዳኖስን ይሻገሩ፤
እነሆ አድምጡ! ውሃ በሚቀዳባቸው ጒድጓዶች ዙሪያ የሚሰማው የብዙ ሰዎች ድምፅ፥ የእግዚአብሔርን ድል ያበሥራል፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ድል አድራጊነት ይናገራል። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ፥ ከከተሞቻቸው ተሰልፈው ወረዱ።