ሐዋርያት ሥራ 5:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሸንጎ አባሎች ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ተቈጥተው ሐዋርያቱን ለመግደል ፈለጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ክፉኛ ተቈጡ፤ ሊገድሏቸውም ፈለጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ሲሰሙ በጣም ተቆጡ፤ ሊገድሉአቸውም አሰቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም በሰሙ ጊዜ ተበሳጩ፤ ጥርሳቸውንም አፋጩ፤ ሊገድሉአቸውም ወደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሲሰሙ በጣም ተቈጡ ሊገድሉአቸውም አሰቡ። |
ሰው የገዛ ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ እንዲሁም አባት የገዛ ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ በጠላትነት ይነሣሉ፤ ለሞትም አሳልፈው ይሰጡአቸዋል።
ስለዚህ ተማሪ እንደአስተማሪው፥ አገልጋይም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። የቤቱን ጌታ ‘ብዔልዜቡል’ ብለው ከጠሩት ቤተሰቦቹንማ ከዚህ በከፋ ስም እንዴት አይጠሩአቸውም!
የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ ዐውቀው በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።
እስከዚህ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ የጳውሎስን ንግግር ያዳምጡ ነበር፤ ከዚህ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦ “እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከምድር ላይ ይወገድ! እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት መኖር አይገባውም!” እያሉ ጮኹ።