ሐዋርያት ሥራ 27:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመርከቡ ውስጥ በጠቅላላው ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሰዎች ነበርን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመርከቡም ላይ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሰዎች ነበርን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመርከቡም ያለን ሁላችን ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ነፍስ ነበርን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመርከቡ ውስጥ የነበሩትም ቍጥራቸው ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ነፍስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመርከቡም ያለን ሁላችን ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ነፍስ ነበርን። |
ማንኛውም ሥልጣን የሚገኘው በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ሆነና አሁን ያሉትም ባለሥልጣኖች የተሾሙት በእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ ሰው ሁሉ ለበላይ ባለሥልጣን መታዘዝ አለበት።
እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።