ሐዋርያት ሥራ 27:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር መካከል ላይ በነፋስ እየተንገላታን ስንሄድ እኩለ ሌሊት ላይ መርከበኞች ወደ ምድር የቀረቡ መሰላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር ላይ ከወዲያ ወዲህ ስንገላታ፣ እኩለ ሌሊት ገደማ መርከበኞቹ ወደ መሬት የተቃረቡ መሰላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዐሥራ አራተኛውም ሌሊት በአድርያ ባሕር ወዲህና ወዲያ ስንነዳ፥ መርከበኞች በእኩለ ሌሊት ወደ አንድ ምድር የቀረቡ መሰላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐሥራ አራተኛውም ቀን በመንፈቀ ሌሊት በአድርያ ባሕር ስንጓዝ ቀዛፊዎች ወደ የብሱ የደረሱ መሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሥራ አራተኛውም ሌሊት በአድርያ ባሕር ወዲህና ወዲያ ስንነዳ፥ መርከበኞች በእኩለ ሌሊት ወደ አንድ ምድር የቀረቡ መሰላቸው። |
የመርከብ አዛዡም ወደ እርሱ ቀርቦ “እንዴት ትተኛለህ? ኧረ እባክህ ተነሥና ወደ አምላክህ ጸልይ፤ ምናልባት ራርቶልን ሕይወታችንን ያድን ይሆናል” አለው።
ስለዚህ የባሕር ጥልቀት መለኪያ ገመድ ሲጥሉ የባሕሩ ጥልቀት አርባ ሜትር ያኽል ሆኖ ተገኘ፤ ጥቂት ቈይተው መለኪያውን እንደገና በጣሉ ጊዜ ሠላሳ ሜትር ያኽል ጥልቀት አገኙ።
መርከበኞቹ ከመርከቡ ወጥተው ለመሸሽ ፈልገው ስለ ነበር በመርከቡ በስተፊት መልሕቆችን የሚጥሉ መስለው በመርከቡ ላይ የነበረችውን ጀልባ ወደ ባሕሩ ጣሉ።
ያን ያኽል ሀብት በአንድ ሰዓት ጠፋ!” ይላሉ። የመርከብ አዛዦች ሁሉ፥ በመርከብ የሚጓዙ ሰዎች ሁሉ፥ በመርከብ ላይ የሚሠሩ ሁሉ፥ በባሕር ላይ የሚነግዱ ሁሉ በሩቅ ይቆማሉ፤