ከዚህ በኋላ መሪዎቹና ሕዝቡ፦ “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ስለ ሆነ ሞት አይገባውም” ሲሉ ለካህናቱና ለነቢያቱ ተናገሩ።
ሐዋርያት ሥራ 25:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ግን በሞት የሚያስቀጣው ምንም በደል አላገኘሁበትም፤ እርሱ ወደ ሮም ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ በማለቱ ወደዚያ ልልከው ወሰንኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ለሞት የሚያበቃ አንዳች ነገር አለማድረጉን ተረዳሁ፤ ሆኖም ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ወደ ሮም ልልከው ወሰንሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን ሞት የሚገባውን ነገር እንዳላደረገ አስተዋልሁ፤ እርሱም ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ እሰደው ዘንድ ቆረጥሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን ለሞት የሚያደርሰው በደል እንዳልሠራ እጅግ መርምሬ፥ እርሱም ራሱ ወደ ቄሣር ይግባኝ ማለትን ስለወደደ እንግዲህ ልልከው ቈርጫለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን ሞት የሚገባውን ነገር እንዳላደረገ አስተዋልሁ፥ እርሱም ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ እሰደው ዘንድ ቈረጥሁ። |
ከዚህ በኋላ መሪዎቹና ሕዝቡ፦ “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ስለ ሆነ ሞት አይገባውም” ሲሉ ለካህናቱና ለነቢያቱ ተናገሩ።
እንዲህም አላቸው፤ “ ‘ሕዝቡን ለሁከት ያነሣሣል’ ብላችሁ ይህን ሰው ወደ እኔ አመጣችሁት፤ እኔም እነሆ፥ በፊታችሁ መርምሬው ካቀረባችሁበት ክስ ሁሉ በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም።
ጲላጦስም “እውነት ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ። ከዚህ በኋላ ጲላጦስ እንደገና ወደ አይሁድ ወጣና እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤
በዚህ ጊዜ ታላቅ ሁካታ ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ የሕግ መምህራንም ተነሡና “እኛ በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት ይሆናል፤ እኛ ምን እናውቃለን?” በማለት ተከራከሩ።
ይሁን እንጂ ስለ እርሱ ለጌታዬ የምጽፈው የተረጋገጠ ነገር የለኝም፤ ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈው ነገር እንዳገኝ ብዬ በፊታችሁ ይልቁንም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! በፊትህ አቅርቤዋለሁ።
ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ ጳውሎስንና ሌሎችንም እስረኞች በአውግስጦስ ክፍለ ጦር ውስጥ ለነበረው ዩልዮስ ለሚባለው መቶ አለቃ አስረከቡአቸው።