ሐዋርያት ሥራ 25:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሳሾቹም ለመናገር አጠገቡ በቆሙ ጊዜ እኔ ክፉ ነገር ሠርቶአል ብዬ የገመትኩትን ያኽል ለክስ የሚያበቃ ምንም ነገር አላቀረቡበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሳሾቹም ተነሥተው በመቆም ሲናገሩ፣ እኔ ያሰብሁትን ያህል ከባድ ክስ አላቀረቡበትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሳሾቹም በቆሙ ጊዜ እኔ ያሰብሁትን ክፉ ነገር ክስ ምንም አላመጡበትም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከሰሱትም በቆሙ ጊዜ፥ እኔ እንደ አሰብሁት በከሰሱት ክስ የሠራው ምንም ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሳሾቹም በቆሙ ጊዜ እኔ ያሰብሁትን ክፉ ነገር ክስ ምንም አላመጡበትም፤ |
ጳውሎስ መልስ ለመስጠት ተዘጋጅቶ ሳለ ጋልዮስ አይሁድን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የአይሁድ ወገኖች! በደል ወይም ከባድ ወንጀል ተፈጽሞባችሁ ቢሆን ኖሮ ክሳችሁን በትዕግሥት በሰማሁ ነበር፤