ሐዋርያት ሥራ 25:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም ብዙ ቀን በመቀመጣቸው ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ እንዲህ ሲል ለንጉሥ አግሪጳ ገለጠ፤ “ፊልክስ አስሮ የተወው እዚህ አንድ ሰው አለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ብዙ ቀን ተቀመጡ፤ ፊስጦስም የጳውሎስን ጕዳይ አንሥቶ ለንጉሡ እንዲህ አለው፤ “ፊልክስ በእስር ቤት የተወው አንድ ሰው እዚህ አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያውም ብዙ ቀን ስለ ተቀመጡ ፊስጦስ የጳውሎስን ነገር ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ገለጠ “ፊልክስ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሱ ዘንድ ብዙ ቀን ከቈዩ በኋላ ፊስጦስ የጳውሎስን ነገር ለንጉሡ ነገረው፤ እንዲህም አለው፥ “ፊልክስ በእስር ቤት ትቶት የሄደ አንድ እስረኛ ሰው በእዚህ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያውም ብዙ ቀን ስለተቀመጡ ፊስጦስ የጳውሎስን ነገር ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ገለጠ፦ “ፊልክስ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ፤ |