ሐዋርያት ሥራ 25:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተነጋገረና “ወደ ሮማ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ካልክ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ትሄዳለህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊስጦስ ከመማክርቱ ጋራ ከተመካከረ በኋላ፣ “ወደ ቄሳር ይግባኝ ስላልህ፣ ወደ ቄሳር ትሄዳለህ!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ “ወደ ቄሣር ይግባኝ ብለሃል፤ ወደ ቄሣር ትሄዳለህ፤” ብሎ መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ፥ “ወደ ቄሣር ይግባኝ ካልህ ወደ ቄሣር ትሄዳለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ፦ “ወደ ቄሳር ይግባኝ ብለሃል፤ ወደ ቄሳር ትሄዳለህ” ብሎ መለሰለት። |
በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።
በደለኛ ከሆንኩ ወይም በሞት የሚያስቀጣ በደል ካደረግሁ ከሞት ልዳን አልልም፤ ነገር ግን የእነርሱ ክስ ከንቱ ከሆነ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም፤ እኔ ወደ ሮማ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ብዬአለሁ።”
እርሱ ግን ጉዳዩ በሮም ንጉሠ ነገሥት እንዲታይለት ፈልጎ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ወደ እዚያ እስክልከው ድረስ በእስር ቤት እንዲቈይ አዘዝኩ።”
ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ ጳውሎስንና ሌሎችንም እስረኞች በአውግስጦስ ክፍለ ጦር ውስጥ ለነበረው ዩልዮስ ለሚባለው መቶ አለቃ አስረከቡአቸው።
በፍጹም እንደማላፍር በተስፋ እጠባበቃለሁ፤ ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና ዛሬ በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።