ጠቡ እየከረረ ስለ ሄደ ሰዎቹ ጳውሎስን እንዳይቦጫጭቁት ፈርቶ አዛዡ “ውረዱና ጳውሎስን ከሰዎቹ መካከል ነጥቃችሁ አምጡ! ወደ ጦሩ ሰፈርም ውሰዱት!” በማለት ወታደሮቹን አዘዘ።
ሐዋርያት ሥራ 23:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ነበር፤ እኔ ግን የሮም ዜጋ መሆኑን ስላወቅሁ ከወታደሮች ጋር ደርሼ አዳንኩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድ ይህን ሰው ይዘው ሊገድሉት ነበር፤ ነገር ግን የሮም ዜጋ መሆኑን ስላወቅሁ፣ ከወታደሮቼ ጋራ ደርሼ አተረፍሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ባሰቡ ጊዜ ከጭፍሮቹ ጋር ደርሼ አዳንሁት፤ ሮማዊ እንደሆነ አውቄ ነበርና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ሰው አይሁድ ያዙት፤ ሊገድሉትም ፈለጉ፤ ከወታደሮችም ጋር ተከላከልሁለት፥ የሮም ሰው መሆኑንም ዐውቄ አዳንሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ባሰቡ ጊዜ ከጭፍሮቹ ጋር ደርሼ አዳንሁት፥ ሮማዊ እንደ ሆነ አውቄ ነበርና። |
ጠቡ እየከረረ ስለ ሄደ ሰዎቹ ጳውሎስን እንዳይቦጫጭቁት ፈርቶ አዛዡ “ውረዱና ጳውሎስን ከሰዎቹ መካከል ነጥቃችሁ አምጡ! ወደ ጦሩ ሰፈርም ውሰዱት!” በማለት ወታደሮቹን አዘዘ።