ሐዋርያት ሥራ 23:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዛዡም የልጁን እጅ ይዞ ገለል አደረገውና “የምትነግረኝ ነገር ምንድን ነው?” ሲል ለብቻው ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዛዡም የጕልማሳውን እጅ ይዞ ለብቻው ገለል በማድረግ፣ “ልትነግረኝ የምትፈልገው ምንድን ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሻለቃውም እጁን ይዞ ፈቀቅ አለና ለብቻው ሆኖ “የምታወራልኝ ነገር ምንድነው?” ብሎ ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሻለቃውም ልጁን በእጁ ይዞ ለብቻው ገለል አድርጎ፥ “የምትነግረኝ ነገሩ ምንድነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሻለቃውም እጁን ይዞ ፈቀቅ አለና ለብቻው ሆኖ፦ የምታወራልኝ ነገር ምንድር ነው? ብሎ ጠየቀው። |
የወይን ጠጅ በመጠጣትም ላይ ሳሉ ንጉሡ “አስቴር ሆይ! ምን እንደምትፈልጊ ንገሪኝ፤ የፈለግሺውን ነገር ሁሉ እፈጽምልሻለሁ፤ የመንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ቢሆን እሰጥሻለሁ” ሲል እንደገና ጠየቃት።
ንጉሡም ንግሥት አስቴርን “እነሆ አይሁድ መናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳ ብቻ እንኳ የገደሉአቸው ሰዎች ቊጥር ዐሥሩን የሃማንን ወንዶች ልጆች ጨምሮ አምስት መቶ ደርሶአል፤ በየሀገሩ የገደሉአቸውማ ከዚህ እጅግ ሳይበልጥ አይቀርም፤ ታዲያ፥ አሁን ከዚህ ሌላ ምን ትፈልጊያለሽ? ይፈጸምልሻል፤ የምትፈልጊውን ንገሪኝ ይሰጥሻል!” አላት።
ይህም ቃል ኪዳን እነርሱን ከግብጽ ለማውጣት እጃቸውን በያዝኩ ጊዜ እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እኔ አምላካቸው ብሆንም እንኳ እነርሱ ቃል ኪዳኔን አልጠበቁም፤ እኔም ችላ አልኳቸው፤
እርሱም ማየት የተሳነውን ሰው እጅ ይዞ እየመራ ከመንደር ወደ ውጪ አወጣው፤ በሰውየውም ዐይኖች ላይ ምራቁን እንትፍ ብሎ እጁን ጫነበትና “አንዳች ነገር ታያለህን?” ሲል ጠየቀው።
ስለዚህ ጳውሎስን ይዘው አርዮስፋጎስ በተባለው ስፍራ ወደሚሰበሰበው ጉባኤ አመጡትና እንዲህ አሉት፤ “ይህ አንተ የምታስተምረው አዲስ ትምህርት ምን እንደ ሆነ ማወቅ እንችላለንን?
የመቶ አለቃውም ልጁን ወደ አዛዡ ይዞ ገባና “እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶኝ ይህ ልጅ ለአንተ የሚነግርህ ነገር ስላለው ወደ አንተ እንዳቀርበው ለመነኝ” አለ።