La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 21:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! እርዱን! ሕዝባችንንና ሕጋችንን፥ ይህንንም ስፍራ እየተሳደበ በየአገሩ ያለውን ሕዝብ ሁሉ የሚያስተምር ይህ ሰው ነው፤ ይህም አልበቃ ብሎት አሕዛብን ወደ ቤተ መቅደስ በማስገባት ይህን የተቀደሰ ስፍራ አርክሶአል!” እያሉ ጮኹ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም እያሉ ጮኹ፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ ርዱን! ሕዝባችንንና ሕጋችንን እንዲሁም ይህን ስፍራ በማጥላላት በደረሰበት ስፍራ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ የሚያስተምረው ሰው ይህ ነው፤ ከዚህም በላይ ግሪኮችን ወደ ቤተ መቅደስ እያስገባ ይህን የተቀደሰ ስፍራ የሚያረክሰው እርሱ ነው።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እየ​ጮ​ሁም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ ርዱን፤ በየ​ስ​ፍ​ራው ሕዝ​ባ​ች​ንን፥ ኦሪ​ት​ንም፥ ይህ​ንም ስፍራ የሚ​ቃ​ወም ትም​ህ​ርት ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እነሆ፥ ይህ ሰው ነው፤ አሁ​ንም አረ​ማ​ው​ያ​ንን ወደ መቅ​ደስ አስ​ገባ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም አረ​ከሰ።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 21:28
9 Referencias Cruzadas  

የኢየሩሳሌም ሕዝብ ጠላቶች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የሕዝቡን ሀብት ዘረፉ፤ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ እንዳይገቡ የተከለከሉ አሕዛብ እንኳ ቤተ መቅደስዋን ሲወሩ ታዩ።


“ነቢዩ ዳንኤል በተናገረው መሠረት የሚያረክሰውን አጸያፊ ነገር በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ባያችሁ ጊዜ አንባቢው ያስተውል!


አንተ በአሕዛብ መካከል የሚኖሩትን አይሁድ ሁሉ ‘ልጆቻችሁን አትግረዙ ወይም ሥርዓቶችን አትፈጽሙ’ እያልክ በማስተማር የሙሴን ሕግ እንዲሽሩ ታደርጋለህ እየተባለ የሚወራውን ሰምተዋል።


በቤተ መቅደስም ያገኙኝ ይህንኑ ሳደርግ ነው፤ በዚያን ጊዜ የመንጻትን ሥርዓት ፈጽሜ ነበር፤ ከእኔ ጋር ብዙ ሕዝብ አልነበረም፤ ሁከትም አልተነሣም።