ስለዚህ ጲላጦስ ይህ ነገር ሁከት እንደሚያስነሣ እንጂ ሌላ ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ ውሃ አስመጥቶ “እኔ ለዚህ ሰው ሞት ኀላፊ አይደለሁም፤ ኀላፊነቱ የእናንተ ነው!” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።
ሐዋርያት ሥራ 18:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ስለ ቃላትና ስለ ስሞች ስለ ሕጋችሁም የምትከራከሩ ከሆነ የራሳችሁ ጉዳይ ነው፤ እኔ በእነዚህ ነገሮች ላይ መፍረድ አልፈልግም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ክርክራችሁ ስለ ቃላትና ስለ ስሞች እንዲሁም ስለ ሕጋችሁ በመሆኑ፣ እናንተው ጨርሱት፤ እኔ በእንዲህ ዐይነት ነገር ፈራጅ ለመሆን አልሻም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ቃልና ስለ ስሞች ስለ ሕጋችሁም የምትከራከሩ ከሆነ ግን፥ ራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ እኔ በዚህ ነገር ፈራጅ እሆን ዘንድ አልፈቅድምና፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ትምህርትና ስለ ስሞች፥ ስለ ሕጋችሁም የምትከራከሩ ከሆነ ግን ለራሳችሁ ዕወቁ፤ እኔ እንዲህ ያለ ነገር ልሰማ አልፈቅድም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ቃልና ስለ ስሞች ስለ ሕጋችሁም የምትከራከሩ ከሆነ ግን፥ ራሳችሁ ተጠንቀቁ እኔ በዚህ ነገር ፈራጅ እሆን ዘንድ አልፈቅድምና አላቸው። |
ስለዚህ ጲላጦስ ይህ ነገር ሁከት እንደሚያስነሣ እንጂ ሌላ ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ ውሃ አስመጥቶ “እኔ ለዚህ ሰው ሞት ኀላፊ አይደለሁም፤ ኀላፊነቱ የእናንተ ነው!” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።
በደለኛ ከሆንኩ ወይም በሞት የሚያስቀጣ በደል ካደረግሁ ከሞት ልዳን አልልም፤ ነገር ግን የእነርሱ ክስ ከንቱ ከሆነ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም፤ እኔ ወደ ሮማ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ብዬአለሁ።”
ወደ ተረትና መጨረሻ ወደሌለው ወደ ትውልዶች ቈጠራ እንዳይመለሱ እዘዛቸው፤ እነዚህ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉ እንጂ በእምነት ለሚደረገው ለእግዚአብሔር ሥራ አይጠቅሙም።
በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያውቅ ነው፤ ነገር ግን ስለ ቃላት የመከራከርና የመጨቃጨቅ ክፉ ምኞት አድሮበታል፤ ይህም የሚያስከትለው ቅንአትን፥ ጠብን፥ ስድብን፥ መጥፎ ጥርጣሬን፥
ነገር ግን ከሞኞች ክርክር፥ ከትውልዶች ቈጠራ፥ ከጭቅጭቅ፥ በሕግ ምክንያት ከሚነሣው ጠብ ራቅ፤ እነዚህ ነገሮች ጥቅም የሌላቸውና ዋጋቢሶች ናቸው።