ሐዋርያት ሥራ 16:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነጋም ጊዜ ባለሥልጣኖቹ “እነዚያ ሰዎች ይለቀቁ” ብለው ፖሊሶችን ላኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲነጋም፣ ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ፈተህ ልቀቃቸው” ብለው መኰንኖቻቸውን ላኩበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነጋም ጊዜ ገዢዎቹ “እነዚያን ሰዎች ፍታቸው፤” ብለው ሎሌዎቻቸውን ላኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋ ጊዜም፥ ገዢዎቹ፥ “እነዚያን ሰዎች ፈትታችሁ ልቀቋቸው” ብለው ብላቴኖቻቸውን ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋም ጊዜ ገዢዎቹ፦ “እነዚያን ሰዎች ፍታቸው” ብለው ሎሌዎቻቸውን ላኩ። |
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ታዲያ ስለምን አታከብሩኝም? በፊቴስ ለምን አትንቀጠቀጡም፤ አሸዋን ውሃ አልፎት እንዳይሄድ ለዘለዓለሙ የባሕር ወሰን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ ባሕር የቱንም ያኽል ቢናወጥ፥ ማዕበል፥ ሞገዱም ቢያስገመግም፥ ወሰን የሆነውን የአሸዋ ግድብ አልፎ መሄድ አይችልም።
“ሰዎች በየምኲራቡ ሲወስዱአችሁ፥ በገዢዎችና በባለሥልጣኖች ፊት ለፍርድ ሲያቀርቡአችሁ ‘ምን እንመልሳለን? እንዴትስ እንናገራለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ።
የሕዝብ አለቆችና የሸንጎው አባሎች ጴጥሮስንና ዮሐንስን የሚያስቀጣ ምንም ምክንያት ባለማግኘታቸው፥ ሕዝቡንም ስለ ፈሩ እንደገና አስጠንቅቀው ለቀቁአቸው፤ ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ በሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያመሰግን ስለ ነበር ነው።