ነገር ግን ወደ ቤቱ እንዲገቡ አጥብቆ ስለ ለመናቸው፥ ከእርሱ ጋር ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚህም በኋላ ሎጥ እንጀራ ጋግረው መልካም ራት እንዲያዘጋጁ ለአገልጋዮቹ ነገራቸው፤ ራትም በተዘጋጀ ጊዜ እንግዶቹ በሉ።
ሐዋርያት ሥራ 16:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷና ቤተ ሰዎቿ ከተጠመቁ በኋላም፣ “በጌታ ማመኔን በርግጥ ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ጥቂት ተቀመጡ” በማለት አጥብቃ ለመነችን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፤” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ከቤተ ሰቦችዋ ጋር ተጠመቀች፤ “ለእግዚአብሔር አማኝ ካደረጋችሁኝስ ወደ ቤቴ ገብታችሁ እደሩ” ብላ ማለደችን፤ የግድም አለችን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን። |
ነገር ግን ወደ ቤቱ እንዲገቡ አጥብቆ ስለ ለመናቸው፥ ከእርሱ ጋር ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚህም በኋላ ሎጥ እንጀራ ጋግረው መልካም ራት እንዲያዘጋጁ ለአገልጋዮቹ ነገራቸው፤ ራትም በተዘጋጀ ጊዜ እንግዶቹ በሉ።
ስለዚህ እባክህ ይህን ያቀረብኩልህን ስጦታ ተቀበለኝ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ሰጥቶኛል” አለ። ስጦታውን እንዲቀበለው ያዕቆብ ዔሳውን አጥብቆ ለመነው። እርሱም ተቀበለው።
አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤
ስለዚህ የቤቱ ጌታ አገልጋዩን እንዲህ አለው፦ ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ገጠር በሚወስዱት ጐዳናዎችና ስላች መንገዶች ሂደህ ሌሎች እንዲመጡ አድርግ!
እነርሱ ግን “ቀኑ መሽቶአል፤ ፀሐይም መጥለቅዋ ነው፤ ስለዚህ ከእኛ ጋር እዚህ ዕደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር ሊያድር ወደ ቤት ገባ።
ነገር ግን ፊልጶስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተናገረውን መልካም ዜና በሰሙ ጊዜ ወንዶችም ሴቶችም አምነው ተጠመቁ።
እኔንና በዚህ ያለውን መላ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስተናግደው ጋይዮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ የከተማይቱ በጅሮንድ የሆነው ኤራስጦስ፥ ወንድማችንም ቋርጦስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። [
እንደ ሞኝ ተናገርኩ! ታዲያ፥ እንዲህ እንድናገር ያደረጋችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ እኔን ማመስገን የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ፤ እኔ ማንነቴ ያልታወቀ ሰው ብሆንም እንኳ ታላላቅ ከተባሉት ሐዋርያት በምንም አላንስም።
አሁን በእስር ቤት ባለሁበት ጊዜና ከመታሰሬም በፊት ለወንጌል እውነት ለመከላከልና እርሱንም ለማጽናት እግዚአብሔር በጸጋው በሰጠኝ ዕድል ሁላችሁም ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ እናንተ ሁልጊዜ በልቤ ናችሁ። ስለዚህም ስለ እናንተ የሚሰማኝ ስሜት ትክክል ነው።
እንግዳ ተቀብሎ ማስተናገድን አትርሱ፤ እንደዚህ እንግዶችን እየተቀበሉ በማስተናገድ አንዳንድ ሰዎች ሳያውቁ መላእክትን ተቀብለው አስተናግደዋል።
ታማኝ ወንድም ነው ብዬ በማስበው በሲላስ አማካይነት ይህን መልእክት ባጭሩ ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍኩላችሁም ልመክራችሁና ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልገልጽላችሁ ብዬ ነው፤ ስለዚህ በዚህ በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንታችሁ ቁሙ።
ሳኦል “ምንም ነገር አልቀምስም” ብሎ እምቢ አለ፤ ይሁን እንጂ ባለሟሎቹም እንዲመገብ አበረታቱት፤ በመጨረሻም “እሺ” ብሎ ከወደቀበት መሬት በመነሣት አልጋ ላይ ተቀመጠ፤