እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ እንዳልሠራን አንተም በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ዘወትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግንብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።”
ሐዋርያት ሥራ 15:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳና ሲላስ ጥቂት ቀኖች እዚያ ከቈዩ በኋላ ከአማኞች ወንድሞች ጋር ተሰነባብተው ወደ ላኩአቸው ተመልሰው ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ጥቂት ጊዜ ከቈዩ በኋላ፣ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ላኳቸው ሰዎች ተመለሱ። [ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱም ዘንድ አያሌ ቀን ከተቀመጡ በኋላ ወንድሞቻቸውን ተሰናብተው በሰላም ወደ ሐዋርያት ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ። |
እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ እንዳልሠራን አንተም በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ዘወትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግንብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።”
ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የትሮ ተመልሶ ሄደና “በግብጽ ወደሚኖሩት ወገኖቼ ተመልሼ ሄጄ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። የትሮም ፈቅዶ “በሰላም ሂድ” አለው።
ከዚህ በኋላ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሁሉ ጋር ሆነው ከጉባኤው መካከል ጥቂት ሰዎችን መርጠው ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ ስለዚህ በወንድሞች መካከል በመሪነት መልካም ዝና የነበራቸውን በርሳባስ የተባለውን ይሁዳንና ሲላስን መረጡ።
ስለዚህ ማንም እንዳይንቀው፤ እርሱ ከወንድሞች ጋር ወደ እኔ እንዲመጣ ስለምጠብቀው ወደ እኔ በሰላም ተመልሶ እንዲመጣ ለጒዞው የሚያስፈልገውን እርዱት።