ሐዋርያት ሥራ 13:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም በሌላ መዝሙር፥ ‘ቅዱሱ ልጅህ መበስበስ እንዲደርስበት አታደርገውም’ ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሌላም ስፍራ፣ “ ‘ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞ በሌላ ስፍራ “ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም፤” ይላልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌላ ስፍራም እንዲህ ይላል፦ ‘ጻድቅህን መፍረስ መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ በሌላ ስፍራ፦ ‘ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም’ ይላልና። |
ሔኖክ ሞት እንዳይደርስበት ወደ ላይ የተወሰደው በእምነት ነው፤ እግዚአብሔር ስለ ወሰደውም አልተገኘም፤ ከመወሰዱ በፊት ደግሞ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታል።