ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 9:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ሌላ ተጨማሪ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ከታላላቅና ከተራ ነጋዴዎች ከሚገባው ቀረጥ ሌላ ነበር። መላው የዐረብ ነገሥታትና አገረ ገዦች ለሰሎሞን ወርቅና ብር ያመጡለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነጋድራሶችና ነጋዴዎች የሚያመጡትን ወርቅ የሚጨምር አልነበረም፤ የዓረብም ነገሥታት ሁሉ የምድሩም ሹማምንት ወርቅና ብር ወደ ሰሎሞን ያመጡ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነጋድራሶችና ነጋዴዎች ከሚያመጡት ሌላ የዓረብ ነገሥታት ሁሉ፥ የምድሩም ሹሞች ወደ ንጉሡ ሰሎሞን ወርቅና ብር ያመጡ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዓረብም ነገሥታት ሁሉ የምድሩም ሹማምት ወርቅና ብር ወደ ሰሎሞን ያመጡ ነበር። |
ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር።
ከፍልስጥኤማውያን አንዳንዶቹ ብዙ ብርና ሌላም ዐይነት ስጦታ ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ ሲያበረክቱ፥ አንዳንድ ዐረቦች ደግሞ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ፍየሎች አመጡለት፤
በሸንበቆዎች ውስጥ የሚኖሩትን እንስሶች ገሥጽ፤ ኰርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጻቸው፤ ሁሉም ተንበርክከው ብራቸውን እንዲያቀርቡልህ አድርግ፤ ጦርነት ማድረግ የሚፈልጉትንም መንግሥታት በትናቸው።