በማግስቱ ብዙ እንስሶችን ዐርደው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡ እንዲመገቡ ሰጡአቸው፤ በተጨማሪም አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ አንድ ሺህ የበግ አውራዎችንና አንድ ሺህ የበግ ጥቦቶችን መሥዋዕት አድርገው በማረድ ሙሉ በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠሉአቸው፤ የወይን ጠጅ መባም አቀረቡ፤
2 ዜና መዋዕል 7:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዐይነት ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺሕ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺሕ በግና ፍየል ሠዋ፤ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ሰሎሞን ሀያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሀያ ሺህ በጎች ሠዋ። እንዲሁ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የጌታን ቤት ቀደሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ዕለት ንጉሡ ሰሎሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችንና መቶ ሃያ ሺህ በጎችን ሠዋ። እንዲሁ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ቅዳሴ አከበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሰሎሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሃያ ሺህ በጎች ሠዋ። እንዲሁ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ። |
በማግስቱ ብዙ እንስሶችን ዐርደው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡ እንዲመገቡ ሰጡአቸው፤ በተጨማሪም አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ አንድ ሺህ የበግ አውራዎችንና አንድ ሺህ የበግ ጥቦቶችን መሥዋዕት አድርገው በማረድ ሙሉ በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠሉአቸው፤ የወይን ጠጅ መባም አቀረቡ፤
ንጉሡም እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን ፊት ለፊት ባለው ከነሐስ በተሠራው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት በማቅረብ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ አንድ ሺህ እንስሶችንም አሳርዶ በመሠዊያው ላይ እንዲቃጠሉ አደረገ።
አሁን እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስን ለመሥራት በመዘጋጀት ላይ ነኝ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እኔና ሕዝቤ በእግዚአብሔር ፊት ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን የምናጥንበት የተቀደሰውን ኅብስት ሳናቋርጥ ለእግዚአብሔር የምናቀርብበት፥ በየቀኑ ጠዋትና ማታ፥ እንዲሁም በሰንበቶች፥ በወር መባቻዎችና በሌሎችም በተቀደሱ በዓላት እግዚአብሔር አምላካችንን ለማክበር የሚቃጠለውን መሥዋዕት የምናቀርብበት የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል፤ የእስራኤል ሕዝብ ይህን ለዘለዓለም እንዲያደርጉ እግዚአብሔር አዞአል።
ንጉሥ ሕዝቅያስ አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ ሰባት ሺህ በጎችንና ፍየሎችን፥ ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች ደግሞ አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ ዐሥር ሺህ በጎችንና ፍየሎችን ዐርደው እንዲበሉ ለሕዝቡ ሰጡ፤ ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ካህናትም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤
ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ሁሉ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ተሰበሰቡ፤ ከዚህም በኋላ ከብዛታቸው የተነሣ ሊቈጠሩ የማይችሉ እጅግ ብዙ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።
ካህናቱም በተመደበላቸው ቦታ ቆሙ፤ ከእነርሱም ፊት ለፊት ሌዋውያን ቆመው አስቀድሞ ንጉሥ ዳዊት አሠርቶ እግዚአብሔርን ለማመስገን ይጠቀምባቸው በነበሩት የዜማ መሣሪያዎች ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በመዘመር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ካህናቱም መለከት ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆመው ነበር።
ለሚቃጠለው መሥዋዕት፥ ለእህል ቊርባንና ለመጠጥ ቊርባን በወር መባቻ፥ በሰንበቶች፥ በተወሰኑትም የእስራኤል ሕዝብ በዓላት እንዲቀርቡ የሚያስፈልጉትን ማዘጋጀት የመሪው ግዴታ ነው፤ ለእስራኤላውያን የኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት፥ የእህሉን ቊርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነትን ቊርባን ማዘጋጀት አለበት።”
በሺህ የሚቈጠሩ አውራ በጎችን ወይም የዐሥር ሺህ ወንዞችን ውሃ የሚያኽል የወይራ ዘይት ባቀርብለት ይደሰት ይሆን? ስለ በደሌና ስለ ኃጢአቴ የበኲር ልጄን ልሠዋለትን?